top of page

ProZ Pro Bono በጨረፍታ

የዚህ ድረ-ገጽ አብዛኛው ክፍል በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ጓደኞቻችን
እና ደንበኞቻችን ስለ ፕሮግራሙ በራሳቸው ቋንቋ ማወቅ እንዲችሉ እድል መስጠት እንፈልጋለን። ከታች
ባለው ገጽ ላይ ፕሮጀክቱ ተሳታፊ የሆኑትን ሰዎች እና ዓላማው ይዳስሳሉ። ይህ ገጽ በአንዳንድ ኮከብ በጎ
ፈቃደኞቻችን ወደተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። በተጨማሪም እርስዎ በማንኛውም ቋንቋ ሊጽፉልን
እንደሚችሉ፣ በጻፉልንም ቋንቋ ምላሽ እንደምንሰጥዎ እባክዎ ይወቁ።

ProZ Pro Bono በጨረፍታ

ምን፣ ማን፣ መቼ፣ የት፣ ለምን?

ምን?
ProZ Pro Bono ፕሮግራም በዓለም ትልቁ የተርጓሚ እና የአስተርጓሚ ባለሙያዎች
ማህበረሰብ በሆነው ProZ.com የተከፈተ ከገንዘብ ነጻ የሆነ የበጎ አድራጎት ተነሳሽነት ነው።
ይህ ፕሮግራም የቋንቋ ባለሞያዎችን` የትርጉም እና የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ከሚፈልጉ
ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር የሚያገናኝ ሲሆን፣ አገልግሎቱም ሙሉ ለሙሉ
በበጎ ፈቃደኝነት የሚሰጥ ይሆናል። ProZ.com በቂ አገልግሎት ያላገኙ ማህበረሰቦች በዚህ
ፕሮግራም አማካኝነት አስፈላጊ መረጃዎችን እና አገልግሎቶችን ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርግ
ዓለም አቀፋዊ የቋንቋ ድጋፍ ትሥሥር ይፈጥራል።

ማን?
ProZ Pro Bono ፕሮግራም በዓለም ዙሪያ ያሉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ለብዝኃ ቋንቋ
ማኅበረሰቦች አገልግሎት እንዲሰጡ፣ ውስን ሀብታቸውንም አቅመ ደካሞችን የማገልገል ዋና
ዓላማቸው ላይ እንዲያውሉ የሚያስችል አገልግሎት ያቀርብላቸዋል።

የት?
ProZ Pro Bono ፕሮግራም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው። በዓለም ዙሪያ
የሚገኙ የቋንቋ ባለሙያዎች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች በፕሮግራሙ መሳተፍ ይችላሉ።

ፕሮግራሙ የ ProZ.com ምናባዊ አገልግሎት አሰጣጥን መሠረት በማድረግ ድንበር ተሻጋሪ
ትብብር መኖር እንዲችል ያደርጋል። በጎ ፈቃደኞች አገልግሎቶቻቸውን መስጠት፣ የአገልግሎቱ
ተጠቃሚዎችም ጂኦግራፊያዊ አካባቢያቸው ሳይወስናቸው የአገልግሎቱን ድጋፍ መጠየቅ
ይችላሉ።

መቼ?
ProZ Pro Bono ፕሮግራም ቀጣይነት ያለው ተነሳሽነት ሲሆን በፕሮግራሙ ላይም ዓመቱን ሙሉ
መሳተፍ ይቻላል። የቋንቋ ባለሞያዎች በማንኛውም ጊዜ መመዝገብ፣ አገልግሎቱን የሚሹ
ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ደግሞ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይችላሉ።
በማንኛውም ጊዜ አገልግሎት የምንሰጥ መሆኑ ከቋንቋ ጋር ለተያያዙ አስቸኳይ ፍላጎቶች አፋጣኝ
ምላሽ መስጠት እንዲቻል ያደርጋል።

ለምን?
ProZ Pro Bono ፕሮግራም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን እና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ወይም
ለማግኘት አስቸጋሪ ለሆኑባቸው የማኅበረሰብ አካላት የቋንቋ ክፍተቶችን የማጥበብ ወሳኝ
ዓላማውን በማሳካት ላይ ይገኛል። ይህም በተርጓሚ እና አስተርጓሚ ኅብረት ውስጥ መተባበር
እና መደጋገፍ ማጎልበትን፣ በዓለም ዙሪያም ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣትን ታላሚ ካደረጉ የ
ProZ.com ዋና እሴቶች ጋር ይጣጣማል። ይህ ፕሮግራም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንዛቤን፣
ተግባቦትን እና የመረጃ ተደራሽነትን የማስተዋወቅ ሰፋ ያለ ተልዕኮን በማሳካት ላይ ይገኛል።
ፕሮግራሙ የቋንቋ ባለሞያዎች በበጎ ፈቃደኝነት ክህሎታቸውን በመስጠት፣ በዓለም ዙሪያ ለተቸገሩ
የማኅበረሰብ ክፍሎች ወሳኝ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ የሚያስችል ርህራሄ የተሞላበት እና ተጽእኖ
መፈጠር የሚችል ተነሳሽነት ነው። በ ProZ Pro Bono ፕሮግራም ውስጥ በጎ ፈቃደኛ ተርጓሚዎች
እና አስተርጓሚዎች ክህሎቶቻቸውን እና እውቀታቸውን የሚያበረክቱት ለግል ጥቅማቸው ሳይሆን፣
የቋንቋ ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ህይወት ላይ በጎ ተጽእኖ ለመፍጠር ነው።

የሀገርዎ ወይም የቋንቋዎ አምባሳደር እንዳለን ለማወቅ የአምባሳደሮችን ገጽ ይመልከቱ!

Translated by Meseret Alemayehu and Yidnekachew Geremew / በመሠረት አለማየሁ እና ይድነቃቸው ገረመው የተተረጎመ

bottom of page